የአጠቃቀም መመሪያ

በ SmellTracker ድረገጽ መሰረት የቤት ውስጥ ሽታዎችን በማሽተት የሽታ ደረጃቸውን ይሰጣሉ።  ዓላማውም በኮቪድ-19 ህመም ወቅት የማሽተት ስሜትን መለወጥ በመከታተል የበሽታውን መነሻ  ዋና የግንዛቤ ምልክቶችን ለማግኘት ነው፡፡  እነዚህን ምልክቶች በደንብ ካዳበርን በኋላ ወደ ድረገጹ ይጨመራሉ፡፡

 

ከዚህ ድረገጽ የሚያገኟቸው ውጤቶች፣ የህክምና ምርመራ ውጤቶች አይደሉም። ስለሆነም በምንም አይነት ሁኔታ የህክምና ምርመራን ሊተኩ አይችሉም። ከዚህ ባገኙት ውጤቶች በመመርኮዝ ምንም አይነት የህክምና ሆነ ሌሎች እርምጃዎችን እንዳይዎስዱ፡፡

 

ከዚህ ላይ እንደምታዩት የዚህ ድረገጽ ውሂብ(ዳታ) በሳይንሳዊ ጽሁፎች ሊታተምና ሊታይ ይችላል። ነገር ግን እነዚህ ጽሁፎች የግል ማንነት መረጃዎችንና መለያዎችን በጭራሽ አያካትቱም፡፡ ስለሆነም በውሂቡ(ዳታው) እና ውሂቡን በሰጡት ሰዎች መካከል ማዛመድ የሚያስችል መንገድ አይኖርም ፡፡ ስለሆነም ይህን ከግምት በማስገባት እባክዎን የሚከተሉትን የአጠቃቀም ውል ያረጋግጡ፡

 

እንዲሳተፉ ይህን ያረጋግጡ፦
ዕድሜዎ ከ 18 ዓመት በላይ ነው
እርጉዝ አይደሉም
  ከአሁን በፊት ለሽታ አለርጂ በጭራሽ አልነበርዎትም ፡፡ ከነበርዎት አይሳተፉ ፡፡
የጤና ችግር፤ ለምሳሌ እንደ አሥም (አሥማ) ያሉ በተደጋግሚ ማሽተትን የሚከለክሉ ችግሮች የለብዎትም። የሕክምና ሁኔታዎ ለመሳተፍ የማይፈቅድልዎ ከሆነ ወይም እርግጠኛ ካልሆኑ አይሳተፉ።
ይህን ድረገጽ ወይም  ውጤቶቹን ለንግድ አገልግሎት እይይጠቀሙባቸውም

 

ምልክት በማድረግ ከዚህ በላይ ያሉትን ሁሉ የተረዱ መሆኑን፤ ደንቦቹን(ውሎቹን) የተቀበሉ መሆኑንና ከዚህ ላይ በተጠቀሱት ሁኔታዎች መሰረት ለመሳተፍ የተስማሙ መሆንዎን ያረጋግጡ።

 

 

The Weizmann Olfaction Group is funded by:

ERCHorizon 2020

 

Social Links

Share on FacebookTweet