ይህ እንዴት እንደሚሰራ

ሲራኖ ደ በርጌራክ (Cyrano de Bergerac) “ትልቅ አፍንጫ የአዋቂ ፣ ትሑት ፣ ተወዳጅ፣ ለጋስ እና ነጻ አስተሳሰብ ያለው ሰው ምልክት ” መሆኑን ገልጸዋል። እኛም የእንዳንዶችን ሰዎች አፍንጫ ፣ ምን ይመስላሉ የሚለውን ሳይሆን እንዴት እንደሚሰሩ ስንመለከት ፣ በእርግጥም ስለ ሰዎቹ ማንነት ብዙ የሚናገሩ መሆኑን ተገንዝበናል። እያንዳንዱ ሰው ልዩ የሆኑ የተለያዩ የማሽተቻ መቀበያ ጂኖች ስላሉት፤ ምን አልባት ሰውየው የተለየ የሽታ ግንዛቤ ሊኖረው ይችላል ፡፡ ይህን ልዩነት የሚያሳይ “የማሽተት ስሜት የጣት አሻራ(olfactory fingerprint)” ብለን የምንጠራው በጣም ከፍተኛ የመለየት ችሎታ ያለው የግንዛቤ ምርመራ አድርገናል፡፡ የእያንዳንዱ የማሽተት ስሜት የጣት አሻራ የእያንዳንዱ ሰው የማሽተት ስሜት ጂኖም መስተዋት ነው ፡፡ እነዚህ የጣት አሻራዎች  ከማሽተቻ ሲስተም ጋር የተያያዙ የጅን  ባህሪያትን፤ ለምሳሌ ያህል የበሽታ መከላከያ ቁጥጥርን ባስመለከተ ሊተነብዩ እንደሚችሉ አሳይተናል።  ስለሆነም ትክክለኛ የሆነ የማሽተት ግንዛቤ ሌሎችን  ከማሽተት ጋር ያልተያያዙ የጅን መረጃዎችንም በክፍተኛ ደረጃ ሊገልጹልን ይችላሉ።

 

የተጠቀምንበትን የስነ ቀመር(አልጎሪዝም) ማዕቀፍ ፤ ሰኩንዶ እና ባልደረቦቹ በብሔራዊ የሳይንስ አካዳሚ (ዩኤስኤ) The National Academy of Sciences (USA) በአሳተሟቸው ጽሁፎች ዘርዝረን ገልፀናል፡፡ ከዚህ ላይ  በነፃ ማወርድ ይቻላል።  ስኒፅና ባልደረቦቹ በኬሚካል ሴንስስ (Chemical Senses) መጽሔት ባሳተሙት ጽሑፍም እንዴት እንደዚህ ዓይነቱን ውሂብ(ዳታ) መጠቀም እንደሚቻል ዘርዝረን ገልፀናል፡፡ ከዚህ ላይ በነፃ ማወርድ ይቻላል። በአሁኑ ጥረታችን ደግሞ የኮቪድ -19 በሽታ ሲጀምር የሚያሳይ የማሽተት ስሜት ግንዛቤ የጣት አሻራ ለመፍጠር እንሞክራለን ፡፡.

 

The Weizmann Olfaction Group is funded by:

ERCHorizon 2020

 

Social Links

Share on FacebookTweet