የግላዊነት መመሪያ

Smelltracker ድረገጽ እንደ ባንኮችና የንግድ መስሪያ ቤቶች በድረገጾቻቸው የዱቤ ወይም ክሬዲት ካርድ መረጃዎችን በመመስጠርና በማስተላለፍ  የሚጠቀሙበትን፤ ደህንነቱ በጥብቅ የተጠበቀ የዝውውር ፕሮቶኮል ወይም  Hypertext Transfer Protocol (HTTPS) የሚባልውን ይጠቀማል። ይህም ወደ ድረገጻችን ወይም ከድረገጻችን ውሂብ(ዳታ) በሚዘዋወርበት ጊዜ በጣም ጥብቅ የሆነ ደህንነትን ይሰጣል።

 

Smelltracker ድረገጽ የእያንዳንዱን የጥናት ሂድት ለመከታተል ጊዚያዊ “ክፍለ-ጊዜ” ወይም የኢንተርኔት ኩኪዎችን ይጠቀማል፡፡ እነዚህ አጫጭር ክፍለ-ጊዜዎች ድረ-አሳሹ እንደተዘጋ ወዲያውኑ ይጠፋሉ፡፡ ኩኪዎቹ በተሳታፊ ሰዎች ማሽኖች(ኮምፒዩተር፣ ሞባይል፣ ወዘተ) ውስጥ በቋሚነት አይቀመጡም ፡፡ Smelltracker የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን አይጠቀምም ፡፡

 

በድረ-ገጹ የተሰበሰበው ውሂብ(ዳታ) ማንም የማያውቀው የተጠቃሚ ቁጥር ይሰጠዋል፡፡ ያስታውሱ፤ በኢሜይል ለሚላኩልዎት መረጃዎች ሚስጥራቸው የተጠበቀ ለመሆኑ ዋስትና የለንም።

 

ድረ-ገጻችንን ሲጎበኙ በእርስዎ ድረ-አሳሽ ላይ “ብቅ-ባይ” ማስታወቂያዎች (በአጋጣሚ በኮምፒዩተርዎ መስኮት ላይ ብቅ የሚሉ ማስታወቂያዎች) ሊታዩ ይችላሉ። ለእንደዚህ ዓይነቱ ማስታወቂያዎች ዋና ምንጮች ሌላ የጎበኟቸው ድረ-ገጾች ውይም በኮምፒዩተርዎ ውስጥ ያሉ የሦሥትኛ-ወገን የኮምፒዩተር ፕሮግራሞች(ሶፍትዌር) ናቸው፡፡ Smelltracker ድረ-ገጻችን ሲጎበኙ በ“ብቅ ባይ” ማስታወቂያዎች ላይ ለሚታዩ ምርቶችና አገልግሎቶች ድጋፍም ሆነ ምክር አይሰጥም ፡፡

 

መመሪያችን በተመለከተ ማንኛውም የሚያሳስብዎት ነገር ካለ ይላኩልን

The Weizmann Olfaction Group is funded by:

ERCHorizon 2020

 

Social Links

Share on FacebookTweet